contact
Home
Sector
communication
SPORT
tourism
high school
>
Register
login
astedader
hospital
Register
login
college
Register
login
simada history
ABOUT US
feedback
GRADE 8
በስማዳ ወረዳ የሚገኙ መምህራን በ2012 በጀት ዓመት በመንግስት ስራዎች መሪ እቅድ ላይ ውይይት አደረጉ፡፡
በስማዳ ወረዳ የሚገኙ መምህራን በ2012 በጀት ዓመት በመንግስት መሪ እቅድ ላይ የደ/ጎን/ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙላቴ አሻግሬ፤ የስማዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪአቶ ጌቴ ደረበዉ፤ የስማዳ ወረዳ አዴፓ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበራ ደሴ በተገኙበት ጥቅምት 14/2012 ዓ/ም ውይይት አድርገዋል፡፡
የ2012 ዓ/ም የመንግስት መሪ እቅድ በስማዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በአቶ ጌቴ ደረበዉ የመነሻ ፁህፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
የዉይይቱ ተሳታፊወች በአሁኑ ሰዓት በሀገራችንም ሆነ በክልላችን የተረጋጋ ሰላም በሌሌበት የልማት ዕቅዶችን መፈጸም አይቻልም ፤የተፈጠረዉን የኑሮ ዉድነት የገበያ ማረጋጋት ስራ በመንግስት በኩል እየተሰራ አይደለም ፤የመምህራን ጥቅማጥቅም ባልተከበረበት የትምህርትን ጥራት ማምጣት አስቸጋሪ ነዉ ፤ የትምህርት ግብአት እጥረት አለ፤ የጤና መድህን ተጠቃሚዎች የመድሃኒይት አቅርቦት እጥረት እየታየነዉ ፤በመሰረተ ልማት መንገድ ፤ዉሀ ፤መብራት ፤የትራፊክ አገልገሎት ክፍተት ይታያል፤ የህግ የበላይነት እየተከበረ አይደለም ፤ የሰኔ 15ቱ የአመራር ጥቃት የምርመራ ዉጤት ለህዝብ ይፋ መሆን አለበት የሚሉ ጥያቄዎችና ሀሳቦች ተነስተዋል፡፡
የመድረኩ መሪዎች በበኩላቸዉ የፓለቲካና የልማት ጉዳዎችን ጎን ለጎን ማስኬድ፤የተሰሩ ስራወችን ጥላሸት ሳንቀባ ጉድለቶችን መሙላት ያስፈልጋል ፤የሰኔ 15 ጥቃት ተጣርቶ ይፋ እሰከሚደረግ በአሉባልታ ዉዥንብር ዉስጥ መግባት ገዳይን ማጀገን ትክክል አይደለም ፤የኑሮ ዉድነቱ ሰዉ ሰራሽ ነዉ ህገወጥ ነጋደወችን ማጋለጥ መረጃ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ህብረተሰቡ ከሀሰት ትርክት ፤ምንጫቸዉ ካልታወቀ መረጃወች ፤ብሄርንና ሀይማኖትን ሽፋን በማድረግ ከሚመጣ ጥቃት መጠንቀቅ እንደሚገባ በመድረኩ ማደማደሚያ ተሰጥቷል፡፡
የስ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ዋ//ጽ/ቤት
ቀን 18/02/2012ዓ.ም
በስማዳ ወረዳ በወገዳ ከተማ በቡቲኮች በመዘዋወር አልባሳትን ሲሰርቁ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
በስማዳ ወረዳ በወገዳ ከተማ በስርቆት ወንጀል ተሰማርተው በቡቲኮች በመዘዋወር አልባሳትን ሲሰርቁ የነበሩ ሁለት ግለሰቦችን ጥቅምት 17/2012 ዓ/ም በግምት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት አካባቢ ጎንደር በር ላይ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የስማዳ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ገልጿል፡፡
ግለሰቦቹ በወገዳ ከተማ ውስጥ በልብስ መሸጫ ቡቲኮች ውስጥ ገዥ መስለው በመዘዋወርና ባለቡቲኮችን በማታለል ለስርቆት አመቺ ተደርጎ በተዘጋጀ ጀሪካ አልባሳትን በመክተት ሲንቀሳቀሱ እንደነበር የገለፁ ሲሆን ከዲያቆን መኳንንት ደሳለኝ ቡቲክ ገዥ መስለው በመግባት ለስርቆት ወደተዘጋጀው ጀሪካን ለመክተት ጥረት ሲያደርጉ ዲያቆን መኳንንት ሊያያቸው በመቻሉ ወዲያዉኑ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ ግለሰቦቹ በሞተር ወደ መገንጠያ አምልጠው ለመሄድ ጥረት ሲያደርጉ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡
ግለሰቦቹ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ለመርማሪ ፖሊስ በሰጡት ቃል በእለቱም ከባህርዳር ተነስተው እንደመጡ የገለፁ ሲሆን የመጡትም ለስርቆት እንደነበር ተናግረዋል፡፡በተጨማሪም ወደ ስማዳ ሲመጡ ክምር ድንጋይ ከተማ ላይ የተሳፈሩበት መኪና በቆመበት ሰዓት መስመር ላይ ልብስ ዘርግቶ በመሸጥ ላይ ከነበረ ግለሰብ 3 አልባሳት መስረቃቸውን ለመርማሪ ፖሊስ በሰጡት ቃል ተናግረዋል፡፡
በስማዳ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ሁለገብ ወንጀል መርማሪ ኦፊሰር ሳጅን እንዳሻው ፈንታ እንደገለጹት ተጠርጣሪዎቹ ገዥ መስለው በየ ቡቲኩ በመንቀሳቀስ ሲሰርቁ እንደነበር በሰጡት ቃል መናገራቸውን ገልፀው የልብስ ባለቡቲኩ ዲያቆን መኳንንት ደሳለኝ በትናንትናው እለት ገዥ መስለው ሌቦች ልብስ ወሰዱብኝ ብለው ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ መሰረት በሞተር ለማምለጥ ጥረት ሲያደርጉ በፀጥታ ሀይሉና በወጣቱ ትብብር ጎንደር በር ላይ ተይዘዋል ብለዋል፡፡መርማሪ ኦፊሰሩ እንደገለጹት ተጠርጣሪዎቹ በኩርት ፔስታል 2700 ብር የሚገመት የህፃናት፣የሴቶችና የወንዶች አልባሳት በጀሪካው 1600 ብር የሚገመት 5 የወንድ ሱሪ ይዘው ነው በቁጥጥር የዋሉት ብለዋል፡፡
በመጨረሻም እነዚህ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ጥቆማ በመስጠት ወጣቶች ትልቅ ሚና ተወጥተዋል ያሉት መርማሪ ኦፊሰሩ በቀጣይም ማህበረሰቡና ወጣቱ ለፀጥታ ሀይሉ ተገቢውን ጥቆማ በመስጠት የሚያደርገውን እገዛ ማስቀጠል አለበት ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የስ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ዋ//ጽ/ቤት
ቀን 18/02/2012ዓ.ም
በስማዳ ወረዳ የሴክተር መስሪያ ቤት ሰራተኞች የድርጅት አባላት በ 2012 በጀት ዓመት
የድርጅትና የመንግስት ስራዎች መሪ እቅድ ላይ የውይይት መድረክ በማካሄድ ላይ ናቸው፡፡በውይይት መድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የስማዳ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስናቀው ቆየው እንደተናገሩት በ 2011 በጀት ዓመት ምን ጥንካሬዎች ነበሩ ምንስ ድክመቶች ነበሩ እነዚህን ድክመቶችስ በምን መልኩ ማስተካከል እንዳለብንና እንደ ክልል እየገጠሙን ያሉትን ፈተናዎች እንዴት ማለፍ እንዳለብን የምንመክርበት መድረክ በመሆኑ ትኩረት መስጠት አለብን ብለዋል፡፡አሁን ላይ እንደ አማራ ክልል ምን አይነት ፈተና ላይ እንዳለን ሁላችንም በመገንዘብና ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በመረዳት ልዩነቶች ቢኖሩም እንኳ ልዩነቶችን ወደ ጎን በመተው አንድ ሁነን በመደማመጥና በመወያየት የመጣብንን ፈተና ማለፍ ይኖርብናል ብለዋል አቶ አስናቀው በመክፈቻ ንግግራቸው፡፡
አሁን የስማዳ ወረዳ አዴፓ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አበራ ደሴ የመነሻ ፅሁፉን በማቅረብ ላይ ሲሆኑ በመቀጠል ሰፊ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃ፡፡
የስ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ዋ/ጽ/ቤት
ቀን 03/02/2012 ዓ/ም
በስማዳ ወረዳ የአይሲቲ ማዕከል በወረዳው ህብረተሰብ አቀፍ የመረጃ ተደራሽነት ተግባር እየፈፀመ መሆኑን ገለፀ፡፡
የኮምፒዩተር መሰረታዊ አጠቃቀም ክህሎትን ለሁሉም የወረዳችን ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ በስፋት እየሰራን እንገኛለን ያሉት የመረጃና መሰረተ ልማት ባለሙያ የሆኑት አቶ እንድሪስ ይሳ ፕላዝማን በመጠቀም ወቅታዊ መረጃዎችን እና ስብሰባዎችን ልምድ ልውውጥ እያደረጉ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ባላሙያው አያይዘው እንደተናገሩት የተለያዩ ሶፍት ወየሮችን በማዳበርና በመጠቀም እንደ ቢኤስሲና የሰዓት ፊርማ ከሲስተም ልማት አንፃር በአስተዳደር ፅ/ቤት በኩል በሙከራ እየተሰራበት እንደሆነ ጠቅሰው በቀጣዮቹ አመታት በሌሎች ሴክተር መ/ቤቶች የሚተገበር መሆኑን አስታውቀዋል፡፡አቶ እንድሪስ ይሳ በኔትወርክ ዝርጋታ ከ15 በላይ ኮምፒዩተሮች በ1 ፕሪንተር እንዲሰሩና ድርጅት ጉዳይ፣መንግስት ኮሙዩኒኬሽንና ግብርና ልማት ፅ/ቤት ኢንተርኔት ተጠቃሚ እንዲሆኑም አድርገናል ብለዋል፡፡
የፀጥታ መዋቅሩ የተሻለ ግንዛቤ ይዞ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እንዲሰራ የአመለካከትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የስማዳ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት በወረዳው ላሉ የፖሊስ አመራሮችና የፖሊስ አባላት ከመስከረም 20 እስከ 23/2012 ዓ/ም ለተከታታይ 4 ቀናት በሀገራዊ፣ክልላዊና በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎች በስልጠናው በበሰጡት አስተያየት በክልሉ እስካሁን ድረስ ትልቅ የፀጥታ ችግር እየተፈጠረና የንፁሃን ዜጎች ህይዎት እያለፈ ነው፡፡በክልሉ በተቀነባበረ ሴራ ትልቅ የፀጥታ ችግር እየተፈጠረ እየታየ የክልሉም ሆነ የፌዴራል መንግስት ውሳኔ ከመስጠት ይልቅ በዝምታ እየታለፉ በመሆኑ ችግሮቹ እየተባባሱ ነው፡፡በቀጣይ የክልሉ መንግስት ለሚፈጠሩ ችግሮች አፋጣኝና ዘላቂ ምላሽ መስጠት ይኖርበታል ብለዋል፡፡
የስማዳ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ኢንስፔክተር ውቤ ካሳው ስልጠናው በዋናነት በፀጥታ መዋቅሩ በሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም በፀጥታው ላይ እያጋጠሙ ባሉ ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልፀው በቀጣይ የፀጥታ መዋቅሩ የተሻለ ግንዛቤ ይዞና ወቅቱን ተረድቶ ያሉ ስጋቶችን በመለየትና እነዚህን ችግሮች የፀጥታ ሀይሉ በምን መልኩ መፍታት እንዳለበት ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ነው ብለዋል፡፡ኃላፊው እንደገለጹት የፖሊስ አባላት ስነ ምግባር በሚፈቅደው መሰረት የሰዎችን ሰብዓዊ መብት ማክበር እንደሚገባ በስልጠናው በትኩረት ተሰጥቷል፡፡በቀጣይ የፀጥታ ሀይሉ ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት ሰፊ ስራ የሚጠበቅበት ሲሆን ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት መከላከል መቻል አለበት፡፡ህብረተሰቡም ለፀጥታ ሀይሉ ተገቢውን እገዛ ማድረግ ይኖርበታል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ስ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ዋ//ጽ/ቤት
ቀን 26/01/2012/ዓ.ም
ጥራት ያለው ጥምህርት ለሁሉም !
የስማዳ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የአሰለሰጣኞች ስልጠና ሰጥቷል፡፡በስልጠናውም ትምህርት ቤቶች ሰባት አባላት ያሉት የግለ ግምገማ ኮሚቴ በማቋቋም የት/ቤቱን አጠቃላይ ሁኔታ መከታተል ይኖርበታል ተብሏል፡፡
በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የመስኖ ስራ ቁልፍ መሳሪያ መሆኑ ተገለፀ፡
በስማዳ ወረዳ በበጋ ወራት ከሁለት ጊዜ በላይ አርሶ አደሩ በመስኖ ተጨማሪ ምርት ማምረት እንዲችል የወንዝ ዉሃ ጠለፋ ስራ እየተሰራ ነው፡፡
በዚህም የሙጌ ወንዝ ፤ አርያት፤ ፈሳስና የዝርጋ ውዶ ወንዞችን የውሀ ጠለፋ ስራ በመስራት በመስኖ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ አየሰራ መሆኑን የስ/ወ/ግ/ል/ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡ፅ/ቤቱ በተያዘው በጀት አመት በፈሳስ ወንዝ 1.2 ሚሊዮን ብር የውሃ ጠለፋ ስራ በመስራት 10 ሄ/ር መሬት ለማልማት እና በዝርጋ ውዶ ወንዝ ደግሞ 4.2 ሚለዮን ብር ተመድቦ 80 ሄ/ር መሬት ማልማት የሚያስችል የውሀ ጠለፋ ስራ እየተሰራ መሆኑን የስ/ወ/ግ/ል/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መዝገበ ተገን ተናግረዋል፡